am_tn/exo/02/13.md

1.4 KiB

• በሁለተኛውም ቀን ወጣ

ሙሴ በማግስቱ እየሆነ ያለውን ነገር ለማየትና ለማጣራት መውጣቱን ለመግለጽ ነው

• በዳዩንም

ጥላቻውን የጀመረውን ወይም ጥፋተኛውን ወይም ጓደኛውን ቀድሞ መምታት የጀመረውን ዕብራዊ ወገኑን ማለት ነው። ይህ አባባል በዕብራውያን ዘንድ የታወቀና በባህሉ የተለመደ አባባል ነው።

• በእኛ ላይ አንተን አለቃ ወይስ ዳኛ ማን አደረገህ?

ይህ ጥያቄ የሚያሳየው ሙሴ በሁለቱ ሰዎች መካከል ጣልቃ በመግባቱ ነገሩን ሳታጣራ ወይም በትክክል ሳትረዳ ለምን አለቃ ትሆናለህ ብሎ ለመገሰጽ የተጠቀመበት አባባል ነው። ይህ አጋናኝ ጥያቄ በመደበኛ ዐረፍተ ነገር ሲተረጎም “አንተ በእኛ ላይ ለመፍረድና መሪ ለመሆን አልተጠራህም” እንደ ማለት ነው።

• ግብፃዊውን እንደገደልኸው ልትገድለኝ ትሻለህን?

ይህ አጋናኝ ጥያቄ የሚያመለክተው ውስጠ ወይራ ወይም አሽሙር ነው። አማራጭ ትርጉሙ፦ ትናንትና አንድ ግብጻዊ እንደገደልክ እናውቃለን፥ እኔን ግን አትገድለኝም” ሊሆን ይችላል።