am_tn/exo/01/08.md

1.2 KiB

• በግብጽ... ተነሳ

ግብጽ የሚለው ቃል የግብጽ ህዝብን የሚያመለክት ነው። የዚህ አማራጭ ትርጉም “የግብጽ ህዝብን የሚገዛ አዲስ ንጉስ ነገሰ” የሚል ነው።

• እርሱም ህዝቡን

የግብጽ ንጉስ ለህዝቡ እንዲህ ብሎ ተናገረ።

• ህዝቡን

በግብጽ ምድር የሚኖሩ ህዝቦች ወይም ግብጻውያንን ማለት ነው።

• ኑ

ይህ አባባል ንጉሱንና እርሱ የሚመራውን ህዝብ ወይም ግብጻውያንን የሚያጠቃላል ነው። “እኛ” የሚለው መደብ መገለጫ ነው።

• ሰልፍም በተነሳብን ጊዜ

“ሰልፍ” የሚለው ጠላት በእኛ ጦርነት ባወጀ ጊዜ ወይም ጠላት ልወጋን በሚመጣበት ጊዜ የሚለውን ሀሳብ ይገልጻል። “ሰልፍ በተነሳብን” ጊዜ የሚለው በሰውኛ ዘይቤ የተገለጸ ነው፤ ምክንያቱም ሰልፍ እንደ ሰው ተነሳ የሚል አገላለጽ የያዘ ነው።

• ከምድሪቱም እንዳይወጡ

እስራኤላውያን ግብጽን ለቀው እንዳይሄዱ ማለት ነው።