am_tn/exo/01/06.md

891 B

• ወንድሞቹ

ወንድሞቹ የተባሉት የዮሴፍ አስር ታላቅ ወንድሞቹና አንድ ታናሽ ወንድሙ ስብስብ ነው

• ልጆች አፈሩ

ልጆችን አፈሩ የሚለው ሀረግ በተለዋጭ ዘይቤ የተጻፌ ነው። በእስራኤላውያን ዘንድ ልጅ መውልድ ከዛፍ ፍሬ ማፍራት ጋር ተነጻጽሮ ቀርቧል። የዚህ አማራጭ ትርጉም “ብዙ ልጆች ወለዱ” ወይም “ብዙ ልጆችን አገኙ” የሚል ነው።

• ምድሪቱም በእነርሱ ሞላች

ይህ በተደራጊ ግስ የተጻፈ ሲሆን በአድራጊ ግስ “እነርሱ ምድርቱን ሞሉ” ማለት ነው።

• እነርሱ

በሶስተኛ መደብ የተጠራው “እነርሱ” የሚለው ቃል “እስራኤላውያንን” ያመለክታል።