am_tn/est/09/26.md

1.7 KiB

እነዚህን ቀናት፣ ፉር ከሚለው ስም በመነሳት ፉሪም ብለው ጠሯቸው

አንድን ነገር ከሌላ አንድ ለነገር በመነሳት መሰየም ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፤ ያም ማለት አንድ አይነት ስም መስጠት ወይም ተመሳሳይ ስም መስጠት ነው፡፡ "እነዚህን ቀናት፣ ፉር ከሚለው ቃል በመነሳት ፉሪም ብለው ጠሯቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ፉሪም

ይህ የአይሁድ ህዝብ በጥንቱ ፋርስ በሐማ ሴራ በአንዲት ቀን ውስጥ ከመደምሰስ እና ከእልቂት የተረፈበት መታሰቢያ በዓል ስያሜ ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

የፉር ስያሜ

"ፉር" ማለት ምን ማለት እንደሆነ በግልጽ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ፉር የሚለው ቃል፣ ‘ዕጣ' ማለት ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆና ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

እነዚህ ቀናት ሊከበሩ እና ሊተሰቡ ይገባል

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "አይሁዳች እነዚህን ቀናት ያከብራሉ ያስቧቸዋልም" (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

በታማኝነት ከማክበር በፍጹም አያቋርጡም

ይህ በአዎንታዊ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ሁሌም በታማኝነት ያከብሩታል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡