am_tn/est/09/23.md

2.0 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ይህ ምንባብ ለፉሪም በዓል መከበር ምክንያት የሆነውን ጉዳይ ለማብራራት የአስቴርን አመዛኙን ታሪክ በአጭሩ ያቀርባል፡፡

የአጋጋዊው የሐመዳቱ ልጅ ሐማ

ይህ ከንጉሡ ሹማምንት አንዱ የሆነው የሐማ ስም እና ገለጻ ነው፡፡ ይህን በአስቴር 3፡1 ላይ እንዴት እንደተረጎሙት ይመልከቱ፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

ፉር አወጣ/ጣለ (ይህ ማለት፣ ዕጣ አወጣ ማለት ነው)

"ፉር" በፋርስ ቋንቋ "ዕጣ" የሚል ቃል ነው፡፡ "ጣለ/አወጣ" የሚለው ሀረግ "ፉር ጣለ/አወጣ" የሚለው ምን ማለት እንደሆነ ያብራራል፡፡

ፉር አወጣ/ጣለ (ይህ ማለት፣ ዕጣ አወጣ ማለት ነው)

ለምን ፉር፣ ወይም ዕጣ ጣለ የሚለው በግልጽ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "አይሁድን ለማጥቃት የተሻለው ቀን የትኛው እንደሆነ ለማወቅ እጣ ጣለ (ዕጣ አወጣ)" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆና ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ነገር ግን ጉዳዩ ወደ ንጉሡ ፊት ስትቀርብ

የዕብራይስጡ ጽሁፍ "አስቴር ግን ንጉሡ ፊት ስትቀርብ" ተብሎም ሊተረጎም ይችላል፡፡ አንዳድ ዘመናዊ ቅጂዎች ይህንን ትረጉም ይመርጡታል፡፡

ሐማ በአይሁዳች ላይ ያወጣው ክፉ እቅድ በገዛ ራሱ ላይ ተመለሰበት

"በራሱ አናት ላይ ተመለሰ" ማለት በሐማ ላይ ይፈጸም ማለት ነው፡፡ "ሐማ በአይሁድ ላይ ያዘጋጀው ክፉ እቅድ በራሱ ላይ መፈጸም አለበት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)