am_tn/est/09/11.md

2.2 KiB

አምስት መቶ ወንዶች

"500 ወንዶች" (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

ፓርሻንዳታ፣ ደልፎን፣ አስፓታ፣ ፓራታ፣ አዳልያ፣ አረዳታ፣ፓርማታ፣ አሪሳይ፣ አሪዳይ፣ ዋይዛታ

እነዚህ የወንዶች ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

አስር ወንድ ልጆች

"10 ወንድ ልጆች" (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

ከዚያ እነርሱ በተቀረው በንጉሡ አውራጃዎች ምን አደረጉ?

ንጉሡ ይህንን ጥያቄ ያነሳው አይሁድ በሌሎች አውራጃዎችም የሚገኙ ጠላቶቻቸውን መግደል እንደለባቸው ማመኑን ለማሳየት ነው፡፡ "በሌሎቹ በንጉሡ ግዛቶች ማድረግ ያለባቸው" ወይም "በተቀሩትም የንጉሡ ግዛቶች ተጨማሪ ብዙ ጠላቶቻቸውን እንዲገድሉ!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሬቶሪካል/ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

አቤቱታሽ/ልመናሽ ምንድን ነው?

"አቤቱታ/ልመና" የሚለው ረቂቅ ስም "ጠየቀ" ወይም "ለመነ" በሚል ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "የምትለምኚው ምንድን ነው?" ወይም "ምን ትፈልጊያለሽ?" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ይሰጥሻል

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "የምትለምኚውን እኔ እሰጥሻለሁ" ወይም "የምጠይቂውን እኔ ለአንቺ አደርገዋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

የምትጠይቂው ምንድን ነው?

"ጥያቄ" የሚለው ረቂቅ ስም "ጠየቀ" ወይም "ፈለገ" በሚል ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ " ምን ትጠይቂያለሽ?" ወይም "ምን ትፈልጊያለሽ?" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)