am_tn/est/09/01.md

3.6 KiB

አዳር በተባለው በአስራ ሁለተኛው ወር፣ በአስራ ሶስተኛ ቀን

በአስቴር 3፡13 ተመሳሳይ የሆነውን ሀረግ እንዴት እንደተረጎሙት ይመልከቱ

የንጉሡ ህግ እና አዋጅ ሊፈጸም ባለበት ወቅት

"ሊፈጸም" የዚህ ፈሊጥ ትርጉም የታዘዘን ወይም የታቀደን ነገር ማድረግ ማለት ነው፡፡ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ሰዎች የንጉሡን ህግና አዋጅ የሚፈጽሙበት ጊዜ ሲደርስ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

በእነርሱ ላይ ስልጣን ለማግኘት

በሰዎች ላይ ሃይል ማግኘት እነርሱን ለማሸነፋቸው ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ "አይሁዶችን ለማሸነፍ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ተቀለበሰ

"ሁኔታው ተቀለብሶ ነበር፡፡" ሁኔታው ተቀልብሶ የሚለው ዘይቤያዊ አነጋገር ትርጉሙ ሊሆን ከሚጠበቀው ተቃራኒው ሲሆን ማለት ነው፡፡ "ተቃራኒው ሆነ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ግዛቶች

ግዛት አንዳንድ አገራት ለአስተዳደር ሲባል የሚከልሉት ሰፊ አካባቢ/ስፍራ ነው፡፡ ይህንን በአስቴር 1፡1 ላይ እንዴት እንደተረጎሙት ይመልከቱ፡፡

የእነርሱን ጥፋት በሚፈልጉ ወገኖች ላይ አደጋ ለመጣል

በሰዎች ላይ አደጋ መጣል የሚለው ከእነርሱ ጋር መዋጋት ለሚለው ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ "ጠላቶቻቸውን ለመዋጋት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት- የሚለውን ይመልከቱ)

በእነርሱ ላይ ጥፋት ለማምጣት የሞከረው ማን ነው

በሰዎች ላይ ጥፋት ማምጣት የሚለው ፈሊጥ ትርጉሙ በእነርሱ ላይ ጥፋት እንዲደርስ ምክንያት መሆን ማለት ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ እነርሱን ማጥፋት የሚለውን ያመላክታል፡፡ "እነርሱን ለማጥፋት የሞከረው ማን ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ማንም ሊቋቋማቸው አልቻለም

ሰዎችን ተቃውሞ መቆም የሚለው የሚወክለው ጥቃታቸውን መቋቋምን ነው፡፡ "ማንም የአይሁዳዊያንን ጥቃት መቋቋም አይችልም" ወይም "ማንም በስኬት ከአይሁዶች ጋር መዋጋት አይችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት- የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱን መፍራት በሁሉም ላይ ህዝቦች ላይ ወደቀ

ፍርሃት በሰዎች ላይ ወደቀ የሚለው የሚወክለው ሰዎች እጅግ ፈሩ የሚለውን ነው፡፡ "ሁሉም ህዝብ አይሁዶችን እጅግ ፈራ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)