am_tn/est/08/09.md

2.0 KiB

የንጉሡ ጸሐፊዎች ተጠርተው ነበር

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ንጉሡ የእርሱን ጸሐፈት ጠራ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ አንባቢ መረዳት የሚገባው ንጉሡ ምናልባት ለአንዱ ሹም ሰነዱን እንዲያመጣ ያዘዘው መሆኑን ነው፡፡ ንጉሡ ሰነዱን እንዲያመጡለት ምናልናት ጮክ ብሎ አልተጣራም ይሆናል፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ እና ይሆና ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ሶስተኛው ወር፣ በኒሳን ወር፣ በወሩ ሃያ ሶስተኛ ቀን በዕብራዊያን ቀን አቆጣጠር "ኒሳን" በተባለው

"ኒሳን" በዕብራዊያን ቀን አቆጣጠር የሶስተኛው ወር ስም ነው፡፡ ሃያ ሶስተኛው ቀን በምዕራባዊያኑ ወር አቆጣጠር ወደ ሰኔ አጋማሽ ላይ ነው፡፡ (የዕብራዊያን ወራት እና ተከታታይነትን የሚያሳዩ ቁጥሮች እና ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚሉትን ይመልከቱ)

አዋጅ ተጻፈ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "አዋጅ ጻፉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

127 ግዛቶች

"አንድ መቶ ሃያ ሰባት ግዛቶች" (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

ግዛቶች

ግዛት አንዳንድ አገራት ለአስተዳደር ሲባል የሚከልሉት ሰፊ አካባቢ/ስፍራ ነው፡፡ ይህንን በአስቴር 1፡1 ላይ እንዴት እንደተረጎሙት ይመልከቱ፡፡

በራሳቸው ጽህፈት ተጻፈ

"በራሳቸው ፊደል ተጻፈ፡፡" በዓለም ዙሪያ የተለያዩ የአጻጻፍ ስርአቶች አሉ፡፡