am_tn/est/08/07.md

2.4 KiB

የሐማ ቤት

ይህ የሚገልጸው ሐማ የነበረውን ሁሉ ነው፡፡ "የሐማ የነበረው ሁሉ" ወይም "መላው የሐማ ንብረት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሲኔክቲኪ/ ዘይቤያዊ አነጋጋር- የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ፤ የሚለውን ይመልከቱ)

የሰው መስቀያ እንጨት

ይህንን በአስቴር 6፡4 እንዴት እንደተረጎሙት መለስ ብለው ይመለከቱ

በንጉሡ ስም… የተጻፈ

አንደን ነገር በንጉሥ ስም መጻፍ በእርሱ ስልጣን መጻፍን ያመላክታል፣ ወይም የእርሱ ወኪል ሆኖ መጻፍን ያሳያል፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት- የሚለውን ይመልከቱ)

በማህተም… የወጣ አዋጅ ሊሻር አይችልም

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "በንጉሱ ቀለበት …ማንም አዋጁን ሊሽር ስለማይችል" ወይም " በቀለበት የታተመውን…ማንም አዋጁን ሊሰርዝ ስለማይችል" (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

በማህተም… የወጣ አዋጅ ሊሻር አይችልም

"አዋጅ" እና "አይቻልም" በሚሉት ቃላት መሃል የተሰጠው መረጃ ንጉሡ የሐማን አዋጅ መሻር ያልቻለበትን ምክንየት ያሳያል፡፡ "ምክንያቱም" በሚለው ቃል በግልጽ የማይችልበት ምክንያት ሊታይ ይችላል፡፡ "ቀደም ሲል የተጻፈውን አዋጅ ልሽር አልችልም፣ ምክንያቱም በንጉሡ ስምና ማህተም ከንጉሡ ቀለበት የታተመ ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆና ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

አስቀድሞ በንጉሡ ስም የወጣ አዋጅ

አንድን ነገር በንጉሥ ስም መጻፍ በእርሱ ስልጣን መጻፍን ያመላክታል፣ ወይም የእርሱ ወኪል ሆኖ መጻፍን ያሳያል፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት- የሚለውን ይመልከቱ)