am_tn/est/07/08.md

2.2 KiB

ወይን ጠጅ በሚታደልበት ጊዜ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "አገልጋዮች ወይን ጠጅ በሚያቀርቡበት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ድንክ አልጋ

ሰው ሊቀመጥበት ወይም ሊጋደምበት የሚችል ተለቅ ያለ የቤት ዕቃ

እኔ እያለሁ በገዛ ቤቴ ንግሥቲቱን ያስነውራልን?

ንጉሡ ይህንን ጥያቄ የተጠቀመበት ሐማ ያደርግ በነበረው ነገር መረበሹን እና መቆጣቱን ለማሳየት ነው፡፡ ይህ ጥያቄ ሙሉ ሃሰብ/መግለጫ ተደርጎ ሊተረጎም ይችላል፡፡ " እኔ ባለሁበት እና በገዛ ቤቴ ንግሥቲቱን ሊያስነውር ጭምር ያስባል!" (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ንግሥቲቱን ያስነውራል

"ንግሥቲቱን ያጠቃል፡፡" ይህ ሐረግ በጨዋ አገላለጽ ጾታዊ መድፈርን መግለጫ ነው፡፡ (አስነዋሪ/ጸያፍ ቃልን ሻል ባለ ቃል መጠቀም/ዩፊምዝም የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ ዐረፍተ ነገር ከንጉሡ አፍ እንደ ወጣ ወዲያውኑ

ንግግሩ ከአፉ እንደ ወጣ የሚለው ንግግርን የሚወክል ሜቶኖሚ (ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት ነው)፡፡ "ንጉሡ ይህንን እንደተናገረ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት- የሚለውን ይመልከቱ)

አገልጋዮች የሐማን ፊት ሸፈኑ

ይህንን ያደረጉት ሐማ እንዲገደል ንጉሡ መፈለጉን ስለተረዱ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ "አገልጋዮቹ የሐማን ፊት መሸፈናቸው እንደሚገደል ምልክት ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ እና ተምሌታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)