am_tn/est/07/06.md

1.4 KiB

በፍርሃት ተዋጠ

"እጅግ ፈራ"

ንጉሡ በቁጣ ብድግ አለ

በቁጣ መሆን የሚለው እጅግ መቆጣትን ለመግለጽ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ "ንጉሡ እጅግ ተቆጥቶ ነበር እናም በቁጣ ብድግ አለ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

ስለ ህይወቱ ንግስት አስቴርን ለመማጸን

"ህይወቱን እንድታድንለት ንግሥት አስቴርን ለመማጸን"

ጥፋት እንደተወሰነበት አየ

እዚህ ስፍራ ማየት የሚገልጸው ማወቅን ወይም መረዳትን ነው፡፡ "ጥፋት እንደተወሰነበት አወቀ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በእርሱ ላይ ከንጉሡ ዘንድ ጥፋት ተወስኖበት ነበር

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ጥፋት" የሚለው ረቂቅ ስም ይበልጥ ተጨባጭ በሆነ "ጠፋ" ወይም "ተገደለ" በሚል ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ " ንጉሱ በእርሱ ላይ ጥፋት እንዲፈጸም ወስኖ ነበር" ወይም "ንጉሡ ሊያጠፋው ወስኖ ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ እና ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)