am_tn/est/07/01.md

1.5 KiB

ሐማ

ይህንን የወንድ ስም በአስቴር3፡1 ውስጥ እንዴት እንደተረጎሙት መለስ ብለው ይመልከቱ፡፡ (ስሞችን እንዴት ይተረጉማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

በዚህ በሁለተኛው ቀን

"በዚህ በበዓሉ ሁለተኛ ቀን"

ወይን ጠጅ እያቀረቡ ሳለ

"አገልጋዮች ወይን እየቀዱ እና እነርሱን እያስተናገዷቸው ሳለ"

ልመናሽ ምንድን ነው

"ልመና" የሚለው ረቂቅ ስም "መጠየቅ" ወይም "መፈለግ" በሚል ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ምን ትጠይቂያለሽ" ወይም "ምን ትፈልጊያለሽ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ለአንቺ ይሰጥሻል

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "የጠየቅሽውን እሰጥሻለሁ" ወይም "የምትጠይቂውን አደርግልሻለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

እስከ መንግሥቴ እኩሌታም ቢሆን ይሰጥሻል

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "የመንግሥቴን እኩሌታ እንኳን ቢሆን ብትጠይቂ፣ እሰጥሻለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)