am_tn/est/03/14.md

1.9 KiB

የደብዳቤው ቅጂ በእያንዳንዱ ግዛት ህግ ተደርጎ ነበር

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "በእያንዳንዱ ግዛት የሚገኙ መኳንንት የደብዳቤውን ቅጅ ህግ አድርገው ተቀብለውት ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ግዛት

ግዛት አንዳንድ አገራት ለአስተዳደር ሲባል የሚከልሉት ሰፊ አካባቢ/ስፍራ ነው፡፡ ይህንን በአስቴር 1፡1 ላይ እንዴት እንደተረጎሙት ይመልከቱ፡፡

በእያንዳንዱ ግዛት ለሁሉም ህዝብ እንዲታወቅ ተደርጎ ነበር

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "በእያንዳንዱ ግዛት ለሚኖረው ህዝብ አሳውቀው ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ ቀን

"ያ ቀን"

አዋጁም ተልኮ ነበር

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እነርሱም አዋጁን ልከው ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ግንብ/ምሽግ

ይህ የቤተመንግሥት ግንብን፣ ጠንካራ ይዞታን ወይም የተመሸገ ከተማን ያመለክታል፡፡ በአስቴር 1፡2 ይህንን እንዴት እንደተረጎሙት ተመልሰው ይመልከቱ፡፡

ሱሳ

የዚህን ስፍራ ስም በአስቴር 1፡2 ላይ እንዴት እንደ ተረጎሙት ይመልከቱ፡፡ (ስሞችን እንዴት ይተረጉማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

ተንጣ ነበር

"በታላቅ ግራ መጋባት ውስጥ ነበረች"