am_tn/est/03/12.md

3.0 KiB

የንጉሡ ጸሐፍት ተሰበሰቡ… ሐማ ያዘዘውን ሁሉ የያዘ አዋጅ ተጻፈ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ንጉሡ ጸሐፍቱን ሰበሰበ … እነርሱ ሐማ ያዘዘውን ሁሉ የያዘ አዋጅ ጻፉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

የመጀመሪያው ወር አስራ ሶስተኛው ቀን

ይህ በዕብራዊያን አቆጣጠር የመጀመሪያው ወር ነው፡፡ አስራ ሶስተኛው ቀን በምዕራባዊያኑ አቆጣጠር ወደ ሚያዝያ መጀመሪያ ላይ ነው፡፡ (የዕብራዊያን ወሮች እና ደረጃን የሚያሳዩ ቁጥሮች)

የንጉሡ ግዛቶች ገዢዎች

"የግዛቶች ገዢዎች፡፡" በአስቴር 1፡1 ውስጥ በተረጎሙት መሰረት ይተርጉሙ፡፡ የተጻፈው በንጉሡ ጠረክሲስ ስም ነበር ደግሞም በእርሱ ማህተም ታትሞ ነበር ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እነርሱ አዋጁን በንጉሡ ጠረክሲስ ስም ጻፉ ሐማም በንጉሡ ቀለበት አተመው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

በ…ስም

እዚህ ስፍራ "ስም" የንጉሡን ስልጣን ይወክላል፡፡ "በ… ስልጣን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት- የሚለውን ይመልከቱ)

ሰነዶቹ በመልዕክተኞች እጅ ተላኩ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ " መልዕክተኞች ሰነዶቹን በእጅ አደረሱ" ወይም "መልዕክተኞች ሰነዶቹን በቀጥታ አደረሱ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

እንዲጠፉ፣ እንዲገደሉ፣ እና እንዲደመሰሱ

እነዚህ ቃላት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፤ ጥፋቱ በሙላት እንዲደረግ ትኩረት የሚሰጡ ናቸው፡፡ "ሙሉ ለሙሉ መደምሰስ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጥንድ ትርጉም/ደብሌት የሚለውን ይመልከቱ)

የአስራ ሁለተኛው ወር አስራ ሶተኛ ቀን

"የአስራ ሁለተኛው ወር አስራ ሶስተኛ ቀን" (ተከታታይነትን የሚያሳዩ ቁጥሮች)

አዳር የትኛው ወር ነው

አዳር" በዕብራዊያን የወር አቆጣጠር አስራ ሁለተኛው እና የመጨው ወር ነው፡፡ በምዕራባዊያኑ አቆጣጠር የየካቲት ወር መጨረሻ እና የመጋቢት መጀመሪያ ነው፡፡ (የዕብራዊያን ወራት እና ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

ዝርፊያ

በሃይል መቀማት