am_tn/est/03/08.md

1.8 KiB

አንድ ህዝብ

" አንድ የህዝብ ወገን" ይህ አይሁድን እንደ አንድ ነገድ ያመላክታል፡፡

ተበትኖ የሚኖር

"በብዙ የተለያዩ ስፍራዎች የሚኖር"

ግዛቶች

ግዛት አንዳንድ አገራት ለአስተዳደር ሲባል የሚከልሉት ሰፊ አካባቢ/ስፍራ ነው፡፡ ይህንን በአስቴር 1፡1 ላይ እንዴት እንደተረጎሙት ይመልከቱ፡፡

የንጉሡ … ንጉሡ

ሐማ ለአክብሮት መግለጫ ምልክትነት ንጉሡን በሶስተኛ መደብ ይናገረዋል፡፡ "የእርሱ … እርሱ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱን መተዉ ለንጉሡ ጠቃሚ አይደለም

"ንጉሡ እነርሱ እንዲተርፉ መፍቀድ የለበትም፡፡" ይህ በአዎንታዊ መልክም ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ንጉሡ ሊያስወግዳቸው ይገባል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

በእነርሱ እጅ… እኔ እመዝናለሁ

እዚህ ስፍራ "እጆች" የሚለው ወንዶች የሚለውን ይወክላል፡፡ "መመዘን" የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር ሲሆን ለእነርሱ መክፈል ማለት ነው፡፡ " ለሰዎቹ …እኔ እከፍላለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሲኔክቲኪ/ ዘይቤያዊ አነጋጋር- የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ፤ እና ፈሊጣዊ አነጋጋር/ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

አስር ሺህ መክሊት ብር

"330 ሜትሪክ ቶን ብር" መጽሐፍ ቅዱሳዊ ገንዘብ እና ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)