am_tn/est/02/22.md

1.7 KiB

ነገሩ ለመርዶክዮስ በተገለጸ ጊዜ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "መርዶክዮስ ምን እንዳሴሩ ባወቀ ጊዜ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ እና ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

በመርዶክዮስ ስም

ይህ ፈሊጥ ነው፡፡ "በመርዶክዮስ ምትክ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡(ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

ዘገባው ተመርምሮ ተረጋገጠ፣ በመሆኑም ሁለቱም ሰዎች በስቅላት ተቀጡ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ንጉሡ መርምሮ ዘገባውን አረጋገጠ፣ ደግሞም አገልጋዮቹ ሁለቱን ሰዎች እንዲሰቅሏቸው ትዕዛዝ ሰጠ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ እና ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

የሰው መስቀያ እንጨት

ይህ ሰዎችን ለመስቀል ያገለግል የነበረ አሰራር ሲሆን፣ የገመዱ አንዱ ጫፍ በመስቀያው እንጨት ላይ ሲታሰር ሌላኛው የገመዱ ጫፍ በሚሰቀሉት ሰዎች አንገት ዙሪያ በማድረግ ይንጠለጠላሉ፡፡ "ሰዎችን ለመስቀል የሚዋቀር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (የማይታወቁትን መተረጎም የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ ጉዳይ ተመዝግቦ ነበር

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እነርሱ ይህንን ጉዳይ መዘገቡ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ እና ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)