am_tn/est/02/19.md

1.7 KiB

ደናግልቱ ለሁለተኛ ጊዜ በአንድነት ተሰብበው በነበረ ወቅት

ይህ ሁለተኛው መሰባሰብ መቼ እና ለምን እንደተደረገ ግልጽ አይደለም፡፡ ለዚህም አንዳንድ ትረጉሞች ክፍሉን ለወጥ አድርገው ያቀርቡታል፡፡ ምናልባትም ባለበት ሁኔታ መተርጎሞ እጅግ የተሻለ ሳይሆን አይቀርም፡፡

ለሁለተኛ ጊዜ

"ለአንድ ተጨማሪ ጊዜ" ወይም "ለተጨማሪ ጊዜ" (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

መርዶክዮስ በንጉሡ በር ይቀመጥ ነበር

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) መርደክዮስ በዚያ የሚቀመጠው አስቴር ምን እያደረገች እንደሆነ በበሩ በኩል ከሚያልፉ ብዙ ሰዎች መስማት ይችል ዘንድ ነው በሚል ሊተረጎም ይችላል ወይም 2) " በንጉሡ በር መቀመጥ" የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር ሲሆን መርዶክዮስ በንጉሡ ስልጣን ተሰጥቶት ነበር ማለት ሊሆን ይችላል፡፡

የንጉሡ በር

"ወደ ንጉሡ ቤተመንግሥት መግቢያ በር"

መርዶክዮስ እንዳዘዛት

መርዶክዮስ ስለ ቤተሰቧ ለማንም እንዳትናገር ነግሯት ነበር

በእነዚያ ቀናት

ይህ በታሪኩ ውስጥ አዲስ ትዕይነትን ያስተዋውቃል፡፡ (አዲስ ትዕይነትን ማስተዋወቅ የሚለውን ይመልከቱ)

ገበታ እና ታራ

እነዚህ የወንዶች ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)