am_tn/est/02/17.md

1.7 KiB

ንጉሡ ወደዳት

ይህ "ፍቅር" የሚለው ቃል አስደሳች/ሮማቲክ አጠቃቀም ነው፡፡

ተቀባይነትን አገኘች፣ በፊቱም ሞገስን አገኘች

እነዚህ ፈሊጦች ተመሳሳይ ነገርን ይገልጻሉ፣ ደግሞም አስቴር ምን ያህል ንጉሡን ደስ እንዳሰኘች ትኩረት ይሰጣሉ፡፡"እጅግ ደስ አሰኘችው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጥ እና ጥንድ ትረጉም የሚሉተን ይመልከቱ)

የእቴጌነት ዘውድ በራሷ ላይ ጫነላት

ንጉሡ ይህንን ያደረገው እርሷን ንግሥት ማድረጉን ለማሳየት ነው፡፡(ተምሳሌታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)

"የአስቴር ክብረ በዓል፣"

ይህ የክብረ በዓሉ ስያሜ መሆኑን መግለጹ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል፡፡ "የአስቴር ክብረ በዓል ብሎ ጠራው፣" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ ( ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ለግዛቶች ከግብር እፎይታን ሰጠ

"ከዚያ እቀድሞ ከግዛቶች ይሰበስብ ከነበረው አነስ ያለ ግብር ሰበሰበ"

ግዛቶች

ግዛት አንዳንድ አገራት ለአስተዳደር ሲባል የሚከልሉት ሰፊ አካባቢ/ስፍራ ነው፡፡ ይህንን በአስቴር 1፡1 ላይ እንዴት እንደተረጎሙት ይመልከቱ፡፡

ንጉሣዊ ልግስና

" ንጉሥ ብቻ ሊያደርገው የሚችለው ልግስና"