am_tn/est/02/12.md

1.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ከቁጥር 12-14 ያለው፣ የንጉሡ ሚስቶች ስለሚሆኑ ሴቶች ያሉ ልምዶችን የሚገልጹ የመረጃ ዳራዎች ናቸው፡፡ (የመረጃ ዳራ የሚለውን ይመልከቱ)

ለሴቶቹ የሚደረጉ ደንቦች ከተፈጸሙ

"ለሴቶቹ መደረግ ያለበት በስርዓቱ መሰረት ከተከናወነ"

የውበት እንክብካቤ

ልጃገረዶቹ ውብ ሆነው እንዲታዩ እና መልካም መዓዛ እንዲኖራቸው የሚደረጉ ነገሮች፡፡

መኳኳያ

በአስቴር 2፡3 ውስጥ የተጠቀሙበትን ያንኑ ቃል ወይም ሀረግ ይጠቀሙ

የምትፈልገው ሁሉ ይሰጣት ነበር

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ-ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡"የምትፈልገውን ሁሉ መውሰድ ትችል ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡(አድራጊ እና ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ቤተመንግሥት

በአስቴር 1፡5 ይህንን እንዴት እንደተረጎሙት መለስ ብለው ይመልከቱ፡፡