am_tn/est/02/05.md

2.2 KiB

አንድ አይሁዳዊ ነበር

ይህ መርዶክዮስን እንደ አዲስ ገጸባህሪይ ያስተዋውቃል፡፡ (አዲስ እና አሮጌ ተሳታፊዎችን ማስተዋወቅ የሚለውን ይመልከቱ)

ሱሳ

የዚህን ከተማ ስም በአስቴር 1፡2 ላይ በተረጎሙት መሰረት ይተርጉሙት፡፡ (ስሞችን እንዴት ይተረጉማሉ የሚለውን ክፍል ይመልከቱ)

የኢያዕር ልጅ የሰሜኢ ልጅ የቂስ ልጅ

"ኢያዕር፣ "ሰሜኢ፣" እና "ቂስ" እነዚህ ወንዶች ሲሆኑ እነርሱም የ"መርዶክዮስ" አባቶች ናቸው፡፡ (ስሞችን እንዴት ይተረጉማሉ፤ የሚለውን ክፍል ይመልከቱ)

ብንያማዊ

"የብንያም ነገድ"

እርሱ ተወስዶ ነበር… የባቢሎን ንጉሥ ማረኮት ነበር

ይህ የመረጃ ዳራ መርዶክዮ ወደ ሱሳ ለመኖር እንዴት እንደመጣ ያብራራል፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ- ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነዖር እርሱን እና ሌሎች ምርኮኞችን ከይሁዳ ነጉሥ ከኢኮንያን ጋር ማረኮ ወሰዳቸው" (የመረጃ ዳራ እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ከኢየሩሳሌም ተማርኮ ነበር

የዕብራይስጡ ትርጉም እዚህ ስፍራ ስለማን እንደሚነገር ግልጽ አላደረገውም፡፡ ምናልባት የመርዶክዮስ ቅድም አያት የሆነው ቂስ ሊሆን ይችላል፡፡ ራሱ መርዶክዮስ ከሆነ ግን አስቴርን በተመለከተ የሆነው ትዕይንቶች ሲፈጸሙ እጅግ አርጅቶ ነበር ማለት ነው፡፡ በርካታ አዳዲስ ትርጉሞች ይህንን ጉዳይ ግልጽ አያደርጉትም፡፡ ጥቂት ትርጉሞች ፣ ዩዲቢን (አንሎክ ዳይናሚክ ባይብል) ጨምሮ ከኢየሩሳሌም የተማረከው መርደኪዮስ እንደሆነ አድርገው ማቅረብን ይመርጣሉ፡፡

ኢኮንያን፣ የይሁዳ ንጉሥ

(ስሞችን እንዴት ይተረጉማሉ የሚለውን ክፍል ይመልከቱ)