am_tn/est/02/03.md

2.2 KiB

አያያዥ ሃሳብ፡

ወጣቶቹ አገልጋዮች ለንጉሡ ገለጻቸውን ቀጠሉ

ንጉሡ… የንጉሡ ሹማምንት… ንጉሡ ቢፈቅድ

አገልጋዮቹ ንጉሡን በሶስተኛ መደብ የሚያናግሩት አክብሮታቸውን ለመግለጽ ነው፡፡ "ማድረግ ያለበት… ሹማምንቱ… ንጉሡ ቢፈቅድ" (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)

ግዛቶች

ግዛት አንዳንድ አገራት ለአስተዳደር ሲባል የሚከልሉት ሰፊ አካባቢ/ስፍራ ነው፡፡ ይህንን በአስቴር 1፡1 ላይ እንዴት እንደተረጎሙት ይመልከቱ፡፡

የሴቶች ቤት/ ሃሬም

የአንድ ወንድ ሚስቶች ከብዙ ሚስቶቹ ጋር የሚኖሩበት ቤት

ግንቡ/ምሽጉ

ይህ የቤተመንግሥት ግንብን፣ ጠንካራ ይዞታን ወይም የተመሸገ ከተማን ያመለክታል፡፡ በአስቴር 1፡2 ይህንን እንዴት እንደተረጎሙት ተመልሰው ይመልከቱ፡፡

ሱሳ

በአስቴር 1፡2 ላይ የዚህን ስፍራ ስያሜ እንዴት እንደተረጎሙት መለስ ብለው ይመልከቱ፡፡ (ስሞችን እንዴት ይተረጉማሉ የሚለውን ክፍል ይመልከቱ)

የሴቶች የበላይ ሃላፊ በሆነው በንጉሡ አገልጋይ በሄጌ እንክብካቤ ስር ይሁኑ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ-ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ " የሴቶች ሃላፊ የሆነው፣ የንጉሡ ሹም ሄጌ፣ እነርሱን ይንከባከባል" (አድራጊ እና ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ሄጌ

ይህ የወንድ ስም ነው፡፡(ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ፤ የሚለውን ይመልከቱ)

የሴቶች መኳኳያ

"መኳኳያ"- እንደ የፊት ዱቄት/ፓውደር፣ ፊትን ለማውዛት የሚረዳ ቅባት/ሎሽን፣ ክሬም/ጭቃ ቅባት የመሰለ ሲሆን ብዙውን ጊዜ ሴቶች ውበታቸውን ለማውጣት በፊታቸው ወይም በአካላቸው ላይ የሚቀቡትነው፡፡