በመኳንንቱ በደረሳት የንጉሡ ቃል መሰረት
ይህ በአድራጊ ዐረፍተ-ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "የንጉሡ ሹማምንት ስለ ንጉሡ ትዕዛዝ በነገሯት ጊዜ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ- ገቢር/ተገቢሮ የሚለውን ይመልከቱ)
በቃሉ
"በትዕዛዙ"
ቁጣው በውስጡ ነደደ
ይህ ጠንካራ የንጉሡ ቁጣ የተገለጸው በውስጡ እንደሚነድ እሳት ነው፡፡ "ቁጣው በውስጡ እንዳለ እሳት የበረታ ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)