1.4 KiB
1.4 KiB
በጠረክሲስ ዘመን
"ጠረክሲስ በሚገዛበት ዘመን" ወይም "ጠረክሲስ ንጉሥ ሆኖ ይገዛ በነበረበት ጊዜ"
ይህ ጠረክሲስ ከህንድ አንስቶ እስከ ኩሽ/ ኢትዮጵያ ድረስ ከ127 ግዛቶች በላይ ይገዛ ነበር፡፡
ይህ የመረጃ ዳራ የቀረበው አንባቢ ጠረክሲስን ለማወቅ ይረዳው ዘንድ ነው፡፡ (የመረጃ ዳራ የሚለውን ይመልከቱ)
ግዛቶች
ግዛት አንዳንድ አገራት ለአስተዳደር ሲባል የሚከልሉት ሰፊ አካባቢ/ስፍራ ነው፡፡
በንጉሣዊ ዙፋኑ ላይ ተቀመጠ
እዚህ ስፍራ "ንጉሣዊ ዙፋን" የሚለው በግዛቱ ላይ ያለውን አገዛዝ የሚያመለክት ሊሆን ይችላል፡፡ "መንግሥቱን አስተዳደረ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት- የሚለውን ይመልከቱ)
ምሽግ/ግንብ
ይህ የቤተመንግሥት ግንብን፣ ጠንካራ ይዞታን ወይም የተመሸገ ከተማን ያመለክታል፡፡
ሱሳ
ይህ የፋርስ ነገስታት መናገሻ ከተማ ነበር (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ፤ የሚለውን ይመልከቱ)