am_tn/eph/06/19.md

1.1 KiB

ኤፌሶን 6፡19-20

አያያዥ ዓረፍተ ነገር፡ ጳውሎስ በእስር ሆኖ ወንጌል በድፍረት እንዲናገር እንዲፀልዩለት ይለምናል፥ለዚህም ደግሞ ቲኪቆስን ያደፋፍራቸው ዘንድ ይልከዋል። ከዚያም ክርስቶስን ለሚወዱ አማኞች ሁሉ በሰላምና በፀጋ ይባርካቸዋል። ቃል ይሰጠኝ ዘንድ፡ ትኩረት፡ "እግዚአብሔር ቃሉን እንዲሰጠኝ" ወይም "እግዚአብሔር መልዕክትን እንዲሰጠኝ" መናገር እንደሚገባኝ በድፍረት እናገር ዘንድ፡ ትኩረት፡ "በድፍረት ገለፃ እንዳደርግ" በሰንሰለት የታሰረ መልእክተኛ የሆንሁት ለዚሁ ነውና፡ ትኩረት፡ "የወንጌል ተወካይ በመሆኔ አሁን በእስር እገኛለሁ" በእስራቴም መናገር እንደሚገባኝ በድፍረት እናገር ዘንድ፡ ትኩረት፡ "የእግዚአብሔርን መልዕክት በድፍረት እንድናገር"