am_tn/eph/02/11.md

1.2 KiB

ኤፌሶን 2፡11-12

አያያዥ ዓረፍተ ነገር፡ ጳውሎስ እነዚህን አማኞች ሊያሳስባቸው የሚፈልገው ነገር አህዛብ እና አይሁድ በክርስቶስ እና በመስቀሉ አማካኝነት አንድ እንደሆኑ ነው። በትውልድ አሕዛብ፡ ከአይሁድ ህዝብ ውጪ የሆነውን ያመለክታል። ያልተገረዙ፡ ከአይሁድ ህዝብ ውጪ የሆኑት በህፃንነታቸው የማይገረዙ ስለነበር በአይሁዶች እግዚአብሔርን እንደማይከተሉ ይቆጠሩ ነበር። መገረዝ ፡ ይህ ቃል የአይሁድ ህዝብ 8 ቀን ከሆነው ወንድ ልጅ ጀምሮ የሚያደርጉትን ግዝረት ያመላክታል። ከክርስቶስ ተለይታችሁ፡ ትኩረት፡ "የማያምኑ" በሰው እጅ የሚከናወነውን መገረዝ፡ ግዝረቱ የሚከናወነው በወንድ ህፃናት አካል ላይ ነው። የእስራኤል ወገን ፡ "የእስራኤል ማህበረሰብ" ለተስፋውም ኪዳን ባዕድ ሆናችሁ፡ ትኩረት፡ "የእግዚአብሔርን የተስፋ ኪዳን አታውቁም ነበር"