am_tn/ecc/09/06.md

1.5 KiB

ፍቅራቸውና ጥላቸው ቅንዓታቸውም

ይህ ሙታን በሕይወት እያሉ ለሌሎች ያሳዩት ፍቅር፣ጥላቻንና ቅንዓትን ይገልፃል፡፡

በሚሰራው ነገር

ይህ በገቢር መልኩ ሊፃፍ ይችላል፡፡ተርጓሚ“ሰዎች የሰሩት ማናኛውም ነገር”

ከፀሃይ በታች

ይህ በምድር ላይ የተደረጉትን ይገልፃል፡፡ የመክብብ 1፡3 ትርጉምን ተመልከት ተርጓሚ “በምድር ላይ”

እንጀራህን በደስታ ብላ ! የወይን ጠጅህንም በተድላ ጠጣ

እነዚህ ሁለቱ ሐረጎች ተመሳሳይ ትርጉም ሲኖራቸው በሕይወት መሠረታዊ ድርጊቶች ( እንቅስቃሴዎች) መርካትን አፅንኦት ይሰጣል፡፡

እንጀራህን

ይህ መብልን ሁሉ ይገልጻል፡፡ ተርጓሚ “መብልህን”

የወይን ጠጅህን በተድላ ጠጣ

እዚህ ጋር “በተድላ” የሚለው ቃል ስሜትን ይገልጻል፡፡ ተርጓሚ የወይን ጠጅህን በደስታ ጠጣ

ሁልጊዜ ልብስህ ነጭ ይሁን ቅባትም ከራስህ ላይ አይታጣ

ነጭ ልብስን መልበስና ቅባትን በራስ ላይ መቀባት ሁለቱም የደስታና የበአል ምልክቶች ነበሩ፡፡

ቅባትም ከራስህ ላይ አይታጣ

ይህ በገቢር መልኩ ሊፃፍ ይችላል፡፡ ተርጓሚ “ራስህን ቅባት ተቀባ”