am_tn/deu/32/42.md

1.1 KiB

ፍላጻዎቼ በደም እንዲሰክሩ አደርጋቸዋለሁ፣ ሰይፌም ከደም ጋር ሥጋን ይበላል

ፍላጻዎች ሰው የሆኑና የሚያሰክር መጠጥ ይሰጣቸው ይመስል እግዚአብሔር ስለ ፍላጻዎቹ ይናገራል፣ ሰይፉም ስለ ራበው ደሙ ተንጠፍጥፎ ያልወጣለትን እንስሳ እንደሚበላ ሰው መስሎ ይናገራል። እነዚህ ዘይቤአዊ አነጋገሮች ብዙ ጠላቶችን ለመግደል ፍላጻዎችንና ሰይፍን የሚጠቀምን ወታደር የሚያመለክቱ ፈሊጣዊ አነጋገሮች ናቸው። ይህ በተራው እግዚአብሔር በጦርነት ውስጥ ጠላቶቹን ስለመግደሉ ዘይቤአዊ አነጋገር ነው።(ዘይቤአዊ አነጋገር፣ ፈሊጣዊ አነጋገር እና ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)

የጠላት አለቆች ከሆኑት ራስ

ሊሆን የሚችለው ትርጉም “በራሳቸው ላይ ረጅም ጸጉር ካላቸው ጠላቶች” የሚለው ነው።