am_tn/deu/32/37.md

1.5 KiB

መጠጊያ ያደረጉ ዐለት፣ አማልክታቸው የት አሉ?

ከሌሎች አማልክት ከለላ ስለመፈለጋቸው የእስራኤልን ሕዝብ እግዚአብሔር ይገስጻቸዋል። ይህ ጥያቄ እንደ ንግግር ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ተመልከቱ፣ እስራኤላውያን እንደሚጠብቋቸው ያሰቧቸው አማልክት ሊረዷቸው አልመጡም” (ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ እና ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የመሥዋዕቶቻቸውን ስብ የበሉ እና የመጠጥ ስጦታ የሆነውን ወይን የጠጡ አማልክት

እዚህ ጋ ለሌሎች አማልክት መሥዋዕት በማቅረባቸው የእስራኤልን ሕዝብ እግዚአብሔር ይገስጻቸዋል። ይህ ጥያቄ እንደ ንግግር ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “እስራኤላውያን ሥጋና ወይን ያቀረቡላቸው አማልክት ሊረዷቸው አልመጡም” (ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

ይነሡና ይርዷችሁ፤ ከለላ ይሁኗችሁ

በእስራኤላውያን ላይ ለማፌዝ እግዚአብሔር ይህንን ይናገራል። እነዚህ አማልክት ሊረዷቸው እንደማይችሉ ያውቃል። አ.ት፡ “እነዚህ ጣዖታት ሊነሡና ሊረዱ ወይም ሊጠብቋችሁ አይችሉም” (ምጸት የሚለውን ተመልከት)