am_tn/deu/32/33.md

1.4 KiB

ወይናቸው የእባብ መርዝና የትናንሽ መርዘኛ እባቦች ጨካኝ መርዝ ነው

ሙሴ የእስራኤል ሕዝብን ጠላቶች መርዘኛ ፍሬና ወይን ከሚያበቅል የወይን ሐረግ ጋር ማነጻጸሩን ይቀጥላል። ይህ ማለት ጠላቶቻቸው ክፉዎች ናቸው። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ትናንሽ መርዘኛ እባቦች

መርዘኛ እባቦች

ይህ ዕቅድ በእኔ በምስጢርነት የተጠበቀ፣ በሀብቴም መካከል ታትሞበት የተቀመጠ አይደለምን?

ይህ ጥያቄ እግዚአብሔር ለእስራኤል ሕዝብ ያለው ዕቅድ ዋጋ እንዳለው ሀብት በምስጢር እንደተጠበቀ አጽንዖት ይሰጣል። ምላሽ የማይፈልገው ጥያቄ እንደ ንግግር ተደርጎ ሊተረጎም ይችላል። ደግሞም፣ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ለእስራኤል ሕዝብና ለጠላቶቻቸው ለማድረግ ያቀድኩትን እኔ አውቃለሁ፣ አንድ ሰው ዋጋ ባላቸው ንብረቶቹ ላይ እንደሚቆልፍባቸው በእነዚያ ዕቅዶች ላይ ቆልፌባቸዋለሁ” (ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)