am_tn/deu/32/23.md

2.5 KiB

ጥፋትን እከምርባቸዋለሁ

በእስራኤላውያን አናት ላይ የሚቆልላቸው ቆሻሻዎች የሆኑ በሚመስል መልኩ በእስራኤላውያን ላይ ስለሚደርስባቸው መጥፎ ነገሮች እግዚአብሔር ይናገራል። አ.ት፡ “ብዙ መጥፎ ነገሮች እንደሚደርሱባቸው አረጋግጣለሁ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ፍላጻዎቼን ሁሉ በእነርሱ ላይ እወነጭፋቸዋለሁ

እዚህ ጋ እግዚአብሔር በእስራኤላውያን ላይ በእርግጠኝነት እንዲደርስባቸው የሚያደርጋቸውን መጥፎ ነገሮች አንድ ሰው በቀስቱ ፍላጻዎችን ከማስወንጨፉ ጋር ያነጻጽራል። አ.ት፡ “እነርሱን ለመግደል ማድረግ የምችለውን ሁሉ አደርጋለሁ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በረሀብ ያልቃሉ

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። የነገር ስም የሆነው “ረሀብ” “ይራባሉ” ወደሚል ግሥ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ይዝላሉ፣ በመራባቸው ምክንያትም ይሞታሉ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ እና የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)

እነርሱ -- ረሀብ እና በሚያቃጥል ሙቀትና በአሰቃቂ ጥፋት ይዋጣሉ

“የሚያቃጥል እሳት” ለሚለው ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) እስራኤላውያን በንዳድ ይሰቃያሉ ወይም 2) በድርቅ ወይም በረሀብ ወቅት የአየሩ ሁኔታ ባለተለመደ መልኩ ሞቃት ይሆናል። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እነርሱ . . . ረሀብ፣ የሚያቃጥል ሙቀትና አሰቃቂ ጥፋት ይውጣቸዋል” ወይም “እነርሱ . . . ረሀብ፣ በሚያቃጥል ሙቀትና በአሰቃቂ ጥፋት ይሞታሉ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

የዱር አራዊትን ጥርስ፣ አፈር ላይ ከሚሳቡ ነገሮች መርዝ ጋር እልክባቸዋለሁ

ጥርስና መርዝ እንስሳው እነዚህን ነገሮች በመጠቀም የሚገድልባቸው ናቸው። አ.ት፡ “እንዲነክሷቸው የዱር አራዊትን፣ ነክሰው እንዲመርዟቸው በአፈር ላይ የሚሳቡትን ነገሮች እልካለሁ” (See: Synecdoche)