am_tn/deu/32/17.md

1.8 KiB

ሠዉ

“የእስራኤል ሕዝብ ሠዉ”

በቅርቡ የመጡትን አማልክት

ይህ ማለት እስራኤላውያን ስለ እነዚህ አማልክት የተማሩት በቅርቡ ነው።

አባቶችህ

ሙሴ ለእስራኤላውያን እንደ ብዙ ሰው ይናገራቸዋል፣ ስለዚህ “የአንተ” የሚለው ቃል ብዙ ቁጥር ነው። (See: Forms of You)

አባትህን -- ትተሃል -- ረስተሃል -- ሰጥቶሃል

ሙሴ እስራኤላውያንን እንደ አንድ ሰው አድርጎ ይናገራቸዋል፣ ስለዚህ “አንተ” እና “የአንተ” የሚልበት አገባብ ሁሉ ብዙ ቁጥር ነው። (See: Forms of You)

ዐለቱን ትተሃል

እዚህ ጋ እግዚአብሔር ብርቱና መከላከያ ስለሆነ ዐለት ተብሎ ተጠርቷል። አ.ት፡ “የእግዚአብሔርን የመከላከል ክብካቤ ትተሃል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ዐለቱ

ይህ ሙሴ ለእግዚአብሔር የሚሰጠው የተጸውዖ ስም እንደ ዐለት ብርቱና ሕዝቡን ለመጠበቅ የሚችል ነው። ይህንን በዘዳግም 32፡4 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

አባትህ የሆነውን -- ልጅ የሰጠህን

ይህ እግዚአብሔርን ከአባትና ከእናት ጋር ያነጻጽራል። ይኸውም፣ እግዚአብሔር በሕይወት እንዲኖሩና ሕዝብ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል ማለት ነው። አ.ት፡ “አባት ያደረጋችሁ … ሕይወትን የሰጣችሁ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)