am_tn/deu/32/15.md

2.1 KiB

ይሹሩን

ሙሴ በሚገባ እንደ ተቀለበና ባለቤቱ ይሹሩን ብሎ እንደሰየመው እንስሳ ስለ እስራኤላውያን ይናገራል። “ ’ይሹሩን’ ማለት ‘ቀጥተኛ የሆነ’ ማለት ነው” የሚል የግርጌ ማስታወሻ ልትጨምርበት ትችላለህ። የአንተ ቋንቋ እስራኤላውያንን እንደ ይሹሩን የማይገልጻቸው ከሆነ የተከፈተው ተለዋዋጭ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም እንደሚያደርገው እስራኤላውያንን እንደ ብዙ ሕዝብ ማመልከት ትችላለህ። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)

መስባቱን ቀጠለ፣ ረገጠም

በሚገባ የተቀለበው እንስሳ፣ ገር ከመሆን ይልቅ የሚራገጠው ይሹሩን እግዚአብሔር ቢንከባከባቸውም እንኳን ያመጹትን እስራኤላውያንን የሚያመለክት ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

መስባትህን ቀጠልክ፣ በጣም ሰብተህ ነበር፣ ፍጆታህን በልተህ ነበር

ሙሴ ለይሹሩን በሚዘምረው መዝሙር እስራኤላውያንን ይገስጻቸዋል። “ሰባችሁ፣ በጣምም ሰባችሁ፣ የሚቻላችሁን ያህልም ሰባችሁ”

የድነቱን ዐለት

ይህ ማለት እግዚአብሔር እንደ ዐለት ብርቱ ነው፣ ሕዝቡን ለመጠበቅም ይችላል ማለት ነው። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ዐለቱ

ይህ ሙሴ ለእግዚአብሔር የሚሰጠው የተጸውዖ ስም እንደ ዐለት ብርቱና ሕዝቡን ለመጠበቅ የሚችል ነው። ይህንን በዘዳግም 32፡4 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እግዚአብሔርን አስቀኑት

እስራኤላውያን እግዚአብሔርን አስቀኑት።