am_tn/deu/32/13.md

1.7 KiB

በምድሪቱ የከፍታ ስፍራ ላይ አስኬደው

ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። “እርሱን” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የእስራኤልን ሕዝብ ነው። አ.ት፡ “እግዚአብሔር በምድሪቱ የከፍታ ስፍራዎች ላይ አስኪዷቸዋል” ወይም “ምድሪቱን እንዲወስዱና እንዲሰፍሩባት እግዚአብሔር ረድቶአቸዋል” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

አስኬደው -- መገበው -- አጠገበው

ሙሴ እስራኤላውያንን እንደ “ያዕቆብ” በመቁጠር መናገሩን ይቀጥላል (ዘዳግም 32፡9-10)። ሙሴ እስራኤላውያንን እንደ ብዙ ሕዝብ አድርጎ እንደተናገራቸው መተርጎም ያስፈልግህ ይሆናል። “አባቶቻችንን እንዲሄዱ አደረጋቸው -- መገባቸው -- አጠገባቸው” (ተውላጠ ስም የሚለውን ተመልከት)

የእርሻውን ፍሬ መገባቸው

“የሚበላው ብዙ ሰብል ወዳለበት ምድር አመጣው”

ከዐለቱ በሚወጣ ማርና ከባልጩታማ ቋጥኝ በሚገኝ ዘይት አጠገበው

ምድሪቱ በዐለት ቀዳዳዎች ውስጥ ማር የሚሠሩ ብዙ የጫካ ንቦች ነበሯት። በተጨማሪም፣ በዐለቶች፣ በኮረብቶችና በተራራዎች ላይ የሚበቅሉ ዘይት የሚሰጡ ብዙ የወይራ ዛፎች ነበሩ።

በማር አጠገበው

ይህ ልክ እናት ለሕፃን ልጇ ጡቷን እንደምትሰጠው ዓይነት ነው። “ማር እንዲጠባ ፈቀደለት” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)