am_tn/deu/32/09.md

1.7 KiB

የእግዚአብሔር ድርሻው ሕዝቡ ነውና፤ ያዕቆብ የርስቱ ዕድል ፈንታው ነው

እነዚህ ሁለት ሐረጎች የሚናገሩት በመሠረቱ አንድ ነገር ነው፣ ስለሆነም ሊጣመሩ ይችላሉ። አ.ት፡ “የያዕቆብ ዘሮች የእግዚአብሕር ርስት ናቸው” (See: Parallelism)

አገኘው -- ጋረደውና ተጠነቀቀለት -- ጠበቀው

“ያዕቆብን አገኘው -- ጋረደውና ተጠነቀቀለት -- ጠበቀው”። ይህንን ምናልባት ሙሴ እንደ ብዙ ሕዝብ አድርጎ የሚናገረው ስለ እስራኤላውያን እንደሆነ መተርጎም ያስፈልግህ ይሆናል። አ.ት፡ “ቅድመ ቅድም አያቶቻችንን አገኛቸው -- ጋረዳቸውና ተጠነቀቀላቸው -- ጠበቃቸው”

ጭው ባለ ምድረ በዳ

እዚህ ጋ “ጭው ያለ” የሚያመለክተው ባዶ መሬት ላይ ነፋሱ ሲነፍስ የሚያሰማውን ድምፅ ነው።

እንደ ዕይኑ ብሌን ጠበቀው

ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። የዐይን ብሌን የሚያመለክተው አንድ ሰው ለማየት የሚያስችለውን በዐይኑ ኳስ ውስጥ ያለውን ጥቁሩን ክፍል ነው። ይህ በጣም አስፈላጊና ጥንቃቄ የሚፈልግ የሰውነት ክፍል ነው። ይህ ማለት የእስራኤል ሕዝብ ለእግዚአብሔር በጣም አስፈላጊና እርሱ ጥበቃ የሚያደርግለትም ነው። አ.ት፡ “በጣም ዋጋ እንዳለውና ውድ ነገር ጠብቆታል”(የአነጋገር ዘይቤ እና Simile የሚለውን ተመልከት)