am_tn/deu/32/07.md

1.9 KiB

ትዝ ይበልህ -- አስብ -- አባትህ -- ያሳዩሃል -- ሽማግሌዎችህ -- ይነግሩሃል

ሙሴ ለእስራኤላውያን እንደ አንድ ሰው አድርጎ ይናገራቸዋል፣ ስለዚህ “አንተ” እና “የአንተ” የሚሉት ቃላት እዚህ ጋ ነጠላ ቁጥሮች ናቸው። (See: Forms of You)

ትዝ ይበልህ

ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “አስታውስ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

የጥንቱን ዘመን

“ከረጅም ዓመታት በፊት”። ሙሴ፣ የእስራኤል ቅድመ ቅድም አያቶች ይኖሩ የነበሩበትን ጊዜ ያመለክታል።

ከብዙ ዓመታት በፊት ስለነበረው ጊዜ አስብ

ይህ ቀደም ሲል በነበረው ክፍል ሙሴ ተናግሮት የነበረው ድጋሚ ነው። ሙሴ የእስራኤል ሕዝብ እንደ ሕዝብ በታሪካቸው ላይ እንዲያተኩሩ ይፈልጋል። (See: Parallelism)

ያሳይሃል

“ግልጽ ያደርግልሃል” ወይም “እንድታስተውለው ያስችልሃል”

ለሕዝቡ ርስታቸውን ሰጣቸው

ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “ሕዝቡ ሊኖሩ በሚገባቸው ስፍራ ላይ አስቀመጣቸው”። “ርስት አድርጎ ወደሚሰጣችሁ” የሚሉ ተመሳሳይ ቃላት በዘዳግም 4፡21 ላይ ይታያሉ። (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

ደግሞም የአማልክታቸውን ቁጥር በሚወስኑበት ጊዜ ለሕዝቦች ድንበሮችን አደረገላቸው

እግዚአብሔር እያንዳንዱን የሕዝብ ወገን ከአማልክቱ ጋር በራሱ ግዛት እንዲኖር ወስኗል። በዚህ መንገድ የሕዝብ ወገኖችን ጣዖታት ተጽዕኖ ገድቧል።