am_tn/deu/32/05.md

2.0 KiB

በእርሱ ላይ በእርኩሰት አድርገዋል

“ትክክል ያልሆነን ነገር በማድረግ ተቃወሙት”። እነዚህን ቃላት በዘዳግም 4፡16 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት።

ወልጋዳና ጠማማ ትውልድ

“ወልጋዳ” እና “ጠማማ” የሚሉት ቃላት በመሠረቱ ትርጉማቸው አንድ ነው። ሙሴ ትውልዱ ምን ያህል ክፉ እንደሆነ አጽንዖት ለመስጠት ይጠቀምባቸዋል። አ.ት፡ “ፈጽሞ ክፉ የሆነ ትውልድ” (See: Doublet)

-ሕዝብ ለእግዚአብሔር በዚህ መንገድ ትመልስለታለህ?

ሙሴ ሕዝቡን ለመገሰጽ ይህንን ጥያቄ ይጠቀማል። አ.ት፡ “-ሕዝብ፣ ለእግዚአብሔር ተገቢውን ምስጋና ማቅረብ አለባችሁ” (ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

አንተ ሞኝና የማትረባ ሕዝብ

“ሞኝ” እና “የማትረባ” የሚሉት ቃላት ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ሲሆኑ ሕዝቡ እግዚአብሔርን ባለመታዘዛቸው ምን ያህል ሞኞች እንደሆኑ አጽንዖት ይሰጣሉ። አ.ት፡ “እጅግ ሞኞች የሆናችሁ ሰዎች” (See: Doublet)

አባትህ -- ፈጥሮሃል -- ሠርቶሃል፣ አጽንቶሃል

ሙሴ ለእስራኤላውያን እንደ አንድ ሰው አድርጎ ይናገራቸዋል፣ ስለዚህ “አንተ” እና “የአንተ” የሚሉት ቃላት እዚህ ጋ ነጠላ ቁጥሮች ናቸው።

የፈጠረህ አባትህ አይደለምን?

ሙሴ ሕዝቡን ለመገሰጽ በጥያቄ መልክ ይጠቀማል። ይህ ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ እንደ ንግግር ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር የፈጠረህ አባትህ ነው” (ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)