am_tn/deu/32/03.md

1.3 KiB

የእግዚአብሔርን ስም ዐውጅ

ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “እግዚአብሔር መልካም መሆኑን ተናገር” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

የአምላካችንን ታላቅነት አሳስቡ

“አምላካችን ታላቅ መሆኑን ሰዎች ማወቃቸውን አረጋግጡ”

ዐለቱ

ይህ እንደ ዐለት ብርቱ እና ሕዝቡን መጠበቅ ለሚችለው ለእግዚአብሔር ሙሴ የሰጠው የተፀውዖ ስም ነው። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ሥራው

“እርሱ የሚያደርገው ሁሉ”

መንገዶቹ ሁሉ ትክክል ናቸው

መንገድ ላይ መራመድ አንድ ሰው ሕይወቱን እንዴት እንደሚኖረው የሚያመለክት ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “ሁሉንም ነገር በትክክለኛ መንገድ አድርጓል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እርሱ ትክክለኛና ቀጥተኛ ነው

እነዚህ ሁለት ቃላት በመሠረቱ የሚሉት አንድ ነገር ሆኖ እግዚአብሔር ፍትሐዊና ትክክለኛውን ነገር እንዳደረገ አጽንዖት ይሰጣሉ። (See: Doublet)