am_tn/deu/32/01.md

1.0 KiB

እናንተ ሰማያት ጆሮአችሁን ስጡ -- ምድርም ትስማ

እዚያ ሆነው ይሰሙ ይመስል እግዚአብሔር ለሰማያትና ለምድር ይናገራል። ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) እግዚአብሔር የሚናገረው በሰማይና በምድር ለሚኖሩት ነው፤ ወይም 2) እግዚአብሔር እንደ ሰው ቆጥሯቸው ለሰማይና ለምድር ይናገራል። (See: Apostrophe)

ትምህርቴ እንደ ዝናብ ይንጠባጠብ፣ በተክሎች ላይ እንደጎርፍ

ይህ ማለት የእርሱን ጠቃሚ ትምህርት ሕዝቡ በትጋት እንዲቀበሉ እግዚአብሔር ይፈልጋል። (See: Simile)

የተጣራ

ጤዛ የሚታይበትን ሂደት የሚገልጽ ቃል በራስህ ቋንቋ ተጠቀም።

ጠል

ቅዝቃዜ ባለበት ጠዋት በቅጠሎችና በሣር ላይ የሚገኝ ውሃ

ለጋ ሣር

“አዲስ ተክሎች”

መጉረፍ

ከባድ ዝናብ