am_tn/deu/31/27.md

2.7 KiB

አመጸኛና አንገተ ደንዳና ሕዝብህ

ሙሴ እንደ አንድ ሰው አድርጎ ለሌዋውያን ይናገራል፣ ስለዚህ “አንተ” የሚለው ቃል ነጠላ ቁጥር ነው። (See: Forms of You)

የአንተ አንገተ ደንዳና

በዘዳግም 9፡6 ላይ “እልኸኛ” የሚለውን እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

ከሞትኩኝ በኋላ ይልቁን እንዴት?

ይህ ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ ሕዝቡ እንዴት ያሉ አመጸኞች እንደነበሩ አጽንዖት ይሰጣል። ይህ እንደ ንግግር ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “እኔ ከሞትኩኝ በኋላ እንኳን በይበልጥ አመጸኛ ትሆናላችሁ” (ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

እነዚህን ቃላት በጆሮአቸው እንድናገር

እዚህ ጋ “በጆሮአቸው” ማለት ሕዝቡን ራሳችውን ማለት ነው። አ.ት፡ “የዚህ መዝሙር ቃሎች እነግራችው ዘንድ” (See: Synecdoche)

በእነርሱ ላይ ምስክር እንዲሆኑ ሰማይና ምድርን እጠራለሁ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ሙሴ ለሚናገረው ምስክሮች እንዲሆኑ በሰማይና በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ይጠራል ወይም 2) ሙሴ እንደ ሰዎች ቆጥሯቸው ለሰማይና ለምድር ይናገራል፣ እርሱ ለሚናገረው ምስክሮች እንዲሆኑም ይጠራቸዋል። ተመሳሳይ ሐረግ በዘዳግም 30፡19 ላይ ይታያል።

ፈጽሞ ራሳችሁን ታረክሳላችሁ

“ሙሉ በሙሉ ስሕተት የሆነውን ታደርጋላችሁ”። እነዚህን ቃላት በዘዳግም 4፡16 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት፡

እኔ ካዘዝኳችሁ መንገድ ዘወር ትላላችሁ

“የሰጠዃችሁን መመሪያ መከተል ታቆማላችሁ”። እነዚህን ቃላት በዘዳግም 9፡12 እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት።

በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነውን

የእግዚአብሔር ፊት የሚወክለው የእግዚአብሔርን ውሳኔ ወይም ምዘና ነው። አ.ት፡ “በእግዚአብሔር ውሳኔ ክፉ የሆነ” ወይም “እግዚአብሔር ክፉ ነው ብሎ የሚቆጥረውን” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በእጆቻችሁ ሥራ አማካይነት

እዚህ ጋ “እጆቻችሁ” ማለት ሕዝቡን ራሳቸውን ማለት ነው። አ.ት፡ “በሠራችሁት ሥራ ምክንያት” (See: Synec- doche)