am_tn/deu/31/17.md

2.1 KiB

ቁጣዬ በእነርሱ ላይ ይነድዳል

እግዚአብሔር ቁጣውን እሳት ከሚለኩስ ሰው ጋር ያነጻጽራል። ይህ እርሱን የሚያስቆጣውን የትኛውንም ነገር በሚያጠፋ በእግዚአብሔር ኃይል ላይ አጽንዖት ይሰጣል። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ቁጣዬን በእነርሱ ላይ አነድዳለሁ” ወይም “በእነርሱ ላይ እቆጣለሁ” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

ፊቴን ከእነርሱ እደብቃለሁ

ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “አልረዳቸውም” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

ይዋጣሉ

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እውጣቸዋለሁ” ወይም “ጠላቶቻቸው እንዲውጡአቸው እፈቅድላቸዋለሁ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

ተዋጡ

ይህ “ፈጽመው ጠፉ” ለሚለው ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ብዙ ጥፋትና መከራ ያገኛቸዋል

ይህ ጥፋቱንና መከራውን እንደ ሰው መስሎ ይገልጻቸዋል። አ.ት፡ “ብዙ ጥፋትና መከራ ይደርስባቸዋል” (ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)

-- መካከል እነዚህ ጥፋቶች የመጡብን?

ይህ ጥፋቱንና መከራውን እንደ ሰው መስሎ ይገልጻቸዋል። ይህ ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ እንደ ንግግር ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “-- መካከል እነዚህ ጥፋቶች እያጠፉኝ ነው” (ሰውኛ እና ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

አምላካችን በመካከላችን አይደለም

“ከእንግዲህ እግዚአብሔር እየጠበቀን አይደለም” ወይም “እግዚአብሔር ለብቻችን ትቶናል”