am_tn/deu/30/11.md

1.3 KiB

ትደርስበት ዘንድ ለአንተ እጅግ ሩቅ አይደለም

አንድ ሰው ቁሳዊ አካል ላይ ሊደርስ እንደሚችል ሁሉ ትዕዛዛቱ አንድ ሰው እንዲያደርግ የሚፈልገውን ከትዕዛዛቱ መረዳት እንደሚቻል ሙሴ ይናገራል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር እንድታደርግ የሚፈልግብህን ለመረዳት በጣም አስቸጋሪ አይሆንብህም” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እናደርገው ዘንድ እንድንሰማው ማን ወደ ሰማይ ወጥቶ ያወርድልናል?

እዚህ ጋ ሙሴ ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄን በመጠቀም የእስራኤል ሕዝብ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ለማወቅ በጣም አስቸጋሪ እንደሚሆንባቸው ማሰባቸው ላይ አጽንዖት ይሰጣል። ይህ ጥያቄ እንደ ንግግር ሆኖ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “አንድ ሰው የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ለመማር ወደ ሰማይ መጓዝ አለበት፣ ከዚያም ልንታዘዛቸው እንችል ዘንድ ምን እንደ ሆኑ ሊነግረን መመለስ አለበት” (ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)