am_tn/deu/30/01.md

2.3 KiB
Raw Permalink Blame History

እነዚህ ነገሮች ሁሉ በመጡብህ ጊዜ

እዚህ ጋ “እነዚህ ነገሮች” የሚያመለክቱት በምዕራፍ 28 29 የተዘረዘሩትን በረከቶችና እርግማኖች ነው። “በመጡብህ” የሚለው ቃል የአነጋገር ዘይቤ ሲሆን ትርጉሙ ሲደርስብህ ማለት ነው። አ.ት፡ “እነዚህ ነገሮች ሁሉ በሚደርሱብህ ጊዜ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

በፊትህ ያስቀመጥኩት

ይህ በፊት ለፊታቸው ያስቀመጠው ዕቃ ይመስል መልኩ ሙሴ ለሕዝቡ ስለ ነገራቸው በረከቶችና እርግማኖች ይናገራል። አ.ት፡ “አሁን ስለነገርኳችሁ ጉዳይ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ትዝ ይበሉህ

ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “አስታውሳቸው” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

በሌሎች ሕዝቦች ሁሉ መካከል

“በሌሎች ሕዝቦች ውስጥ በምትኖርበት ጊዜ”

አውጥቶሃል

“እንድትሄድ አስገድዶሃል”

ድምፁን ታዘዘው

እዚህ ጋ “ድምፅ” የሚያመለክተው እግዚአብሔር የሚናገረውን ነው። አ.ት፡ “እርሱ የሚለውን ታዘዝ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በሙሉ ልብህና በሙሉ ነፍስህ

እዚህ ጋ “ልብ” እና “ነፍስ” የአንድን ሰው ውስጣዊ ማንነት የሚያመለክቱ ፈሊጣዊ አነጋገሮች ናቸው። እነዚህ ሁለቱ ሐረጎች በአንድ ላይ “ፍጹም” ወይም “በቅንነት” ለማለት ጥቅም ላይ ውለዋል። እነዚህን ቃላት በዘዳግም 4፡29 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት። (ፈሊጣዊ አነጋገር እና Doublet የሚለውን ተመልከት)

ምርኮኛነትህን ይቀይረዋል

“ከምርኮኝነት ነጻ ያወጣሃል”። የነገር ስም የሆነው “ምርኮኝነት” እንደ ግሳዊ አንቀጽ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ከማረኩህ ከእነርሱ ነጻ ያወጣሃል” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)