am_tn/deu/29/27.md

1.9 KiB

የእግዚአብሔር ቁጣ በዚህች ምድር ላይ ነዷል

ሙሴ የእግዚአብሔርን መቆጣት ከአንድ እሳት ከሚለኩስ ሰው ጋር ያነጻጽራል። ይህ እግዚአብሔር እርሱን የሚያስቆጣውን የትኛውንም ነገር ስለሚያጠፋበት ኃይሉ አጽንዖት ይሰጣል፤ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር አይችልም። አ.ት፡ “እግዚአብሔር በዚህች ምድር ላይ በጣም ተቆጥቷል” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

በዚህች ምድር ላይ እንዲያመጣባት

እዚህ ጋ “ምድር” ሕዝቡን የሚወክል ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “ያመጣባቸው ዘንድ የዚህ ምድር ሰዎች” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የተጻፉትን

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እኔ የጻፍኩትን” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

እግዚአብሔር ከምድራቸው ነቅሏቸዋል -- ጥሎአቸዋል

እስራኤል እግዚአብሔር ከአትክልት ስፍራ ነቅሎ ከጣለው መጥፎ ተክል ጋር ተነጻጽሯል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ከምድራቸው አስወግዷቸዋል -- እንዲሄዱም አስገድዷቸዋል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በንዴት፣ በቁጣና በታላቅ መዓት

በመሠረቱ “ንዴት”፣ “ቁጣ” እና “መዓት” የሚሉት ቃላት ትርጉማቸው ተመሳሳይ ሲሆን በእግዚአብሔር ቁጣ ታላቅነት ላይ አጽንዖት ይሰጣሉ። አ.ት፡ “እጅግ ታላቅ በሆነ ቁጣው” ወይም “እጅግ ስለተቆጣ” (See: Doublet)