am_tn/deu/29/22.md

2.9 KiB

የሚመጣው ትውልድ፣ ከእናንተ በኋላ የሚነሡት ልጆቻችሁ

“ከእናንተ በኋላ -- ልጆቻችሁ” የሚሉት ቃላት “የሚመጣው ትውልድ” ማን መሆኑን ይናገራሉ።

በዚህች ምድር ላይ የሆኑት መቅሰፍቶችና እግዚአብሔር እንዲታመሙበት ያደረጋቸው በሽታዎች

“እግዚአብሔር የከነዓንን ምድር በመቅሰፍትና በበሽታ እንዴት እንደረገማት”

ምድሩ ሁሉ ዲንና የሚቃጠል ጨው ሆነው በሚያዩበት ጊዜ

ሰዎች መሬቱ ምንም ነገር እንዳያበቅል ዲንና ጨው ያደርጉበታል። “እግዚአብሔር ምድሪቱን በዲንና በጨው እንዳቃጠላት በሚያዩበት ጊዜ”

ምንም ነገር የማይዘራበት ወይም ፍሬ የማያፈራበት ስፍራ

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ማንም ዘር ሊዘራበት የማይችልበትና ሰብሉ ፍሬ የማያፈራበት ስፍራ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

ሰዶምና ገሞራ እንደ ተገለበጡ

“ተገለበጡ” የሚለው የነገር ስም እንደ አንቀጽ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ሰዶምንና ገሞራን ፈጽሞ እንዳጠፋቸው ጊዜ”

አዳማ እና ሲባዮ

እነዚህ እግዚአብሔር ከሰዶምና ገሞራ ጋር ያጠፋቸው ከተሞች ስሞቻቸው ናቸው።(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)

በንዴቱና በመዓቱ

የነገር ስም የሆኑት “ንዴት” እና “ቁጣ” በመሠረቱ ትርጉማቸው አንድ ነው፣ በመሆኑም እንደ ቅጽላዊ ሐረግ ሆኖ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “በጣም በተቆጣ ጊዜ” (See: Doublet)

ከሌሎች ሀገሮች ሁሉ ጋር በመሆን --ምንድነው? በማለት ይናገራሉ

ይህ ቀጥተኛ እንዳልሆነ ትዕምርተ ጥቅስ ሆኖ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ከሌሎች ሀገራት ሁሉ ጋር በመሆን እግዚአብሕር በምድሪቱ ላይ ይህንን ለምን እንዳደረገና ይህ የቁጣው ግለትስ ትርጉሙ ምንድነው በማለት ይጠይቃሉ” (ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆነ ትዕምርተ ጥቅስ የሚለውን ተመልከት)

ከሌሎች ሀገሮች ሁሉ ጋር በመሆን -- ይናገራሉ

“ዘሮቻችሁና የሌሎች ሀገራ ሰዎች ሁሉ -- ይላሉ”

ይህ የታላቅ ቁጣ ግለት ትርጉሙ ምንድነው?

ጸሐፊው በሁለት ቃላት አማካይነት የሚያስተላልፈው አንድ አሳብ ነው። አ.ት፡ “የዚህ አስፈሪ ቁጣ ትርጉሙ ምንድነው?” (See: Hendiadys)