am_tn/deu/29/20.md

1.5 KiB

የእግዚአብሔር ቁጣና ቅንዓት ይነዳል

ልክ እሳት በኃይል እንደሚነድ የእግዚአብሔር ቁጣና ቅንዓትም በኃይል ሊነድ ይችላል። አ.ት፡ “የእግዚአብሔር የቅንዓቱ ቁጣ እንደ እሳት ይግላል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የእግዚአብሔር ቁጣና ቅንዓቱ

እዚህ ጋ “ቅንዓት” የሚለው ቃል “የእግዚአብሔርን ቁጣ” ያብራራል። አ.ት፡ “የእግዚአብሔር የቅንዓቱ ቁጣ” (See: Hen- diadys)

የተጻፉትን

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እኔ የጻፍኩትን” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

በዚህ መጽሐፍ የተጻፉት እርግማኖች ይመጡበታል

ሙሴ እርግማኖቹን በድንገት በሚያጠቃቸው ሰው መስሎ ይገልጻቸዋል። እነዚህን ቃላት በዘዳግም 28፡15 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት። (ዘይቤአዊ አነጋገር እና ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)

እግዚአብሔር ስሙን ከሰማይ በታች ይደመስሰዋል

ይህ ማለት እግዚአብሔር ሰውየውንና ቤተሰቡን ፈጽሞ ያጠፋቸዋል። ወደፊት ሰዎች አያስታውሱትም። በዘዳግም 7፡24 ላይ ተመሳሳይ ሐረግ ይታያል።