am_tn/deu/29/17.md

2.6 KiB

ዛሬ ከአምላካችን ከእግዚአብሔር ልቡ የሚመለስ

እዚህ ጋ “ልብ” የሚያመለክተው ሙሉውን ሰው ሲሆን “መመለስ” ማለት መታዘዝን ማቆም ነው። አ.ት፡ “ከእንግዲህ አምላካችንን እግዚአብሔርን የማይታዘዝ” (See: Synecdoche)

የትኛውም መራራ መርዝ የሚያበቅል ሥር

ሙሴ በድብቅ ሌላ አምላክ ስለሚያመልክ ሰው ሲናገር እርሱን እንደ ሥር እና ያንን አምላክ ለማገልገል የሚሠራውን ክፉ ሥራና ሌሎችም እንዲያደርጉት የሚያበረታታውን ሰዎችን እንደሚመርዝ መራራ እጽዋት ቆጥሮ ይናገራል።(ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ያ ሰው

በቁጥር 18 የተገለጸው ሰው ነው።

በልቡ ራሱን የሚባርክ

ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “ራሱን እንኳን ደስ ያለህ የሚል” ወይም “ራሱን የሚያበረታታ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

በልቤ ግትርነት ብመላለስም

ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “እግዚአብሔርን ለመታዘዝ እምቢ እያልኩኝም እንኳን” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

ይህ እርጥቡን ከደረቁ ጋር የሚያጠፋ ይሆናል

እዚህ ጋ “እርጥብ” እና “ደረቅ” የሚሉት ቃላት ጻድቅና ክፉ የሆኑትን ሰዎች የሚያመለክት ዘይቤአዊ አነጋገሮች ናቸው። ይህ “እያንዳንዱን” የሚል ጥምረት ይፈጥራል። አ.ት፡ “ይህ እግዚአብሔር በምድሪቱ የሚኖሩትን ጻድቅና ክፉ የሆኑትን ሁለቱንም ዓይነት ሰዎች እንዲያጠፋቸው ያደርገዋል” (See: (ዘይቤአዊ አነጋገር እና Merism የሚለውን ተመልከት))

እርጥብ -- ደረቅ

እነዚህ ስማዊ ቅጽሎች እንደ ስም ሊተረጎሙ ይችላሉ። አብዛኛውን ጊዜ ምድሪቱ ደረቅ ስለምትሆንና ሰዎች ሰብላቸው እንዲበቅል ዝናብ ስለሚፈልጉ እነዚህ ቃላት “ሕያው - ምውት” ወይም “ጥሩ -- መጥፎ” ለሚሉት ዘይቤአዊ አነጋገሮች ናቸው። አ.ት፡ “እርጥብ ነገሮች -- ደረቅ ነገሮች” ወይም “ጥሩ ሰዎች -- መጥፎ ሰዎች” (ስማዊ ቅጽል እና ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)