am_tn/deu/29/02.md

2.2 KiB

እግዚአብሔር በዐይኖቻችሁ ፊት ያደረገውን ሁሉ አይታችኋል

እግዚአብሔር ያደረገውንና እነርሱም ያዩትን እንዲያስታውሱ እግዚአብሔር ይጠብቅባቸዋል። እዚህ ጋ “ዐይኖች” ሙሉውን ሰው የሚወክሉ ሲሆኑ ሰውየው ባየው ነገር ላይ አጽንዖት ይሰጣል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ያደረገውን እንድታዩና እንድታስታውሱ እርሱ ያደረገውን ሁሉ አይታችኋል። (See: Synecdoche)

ዐይኖቻችሁ ያዩአቸው ታላላቅ መከራዎች

እዚህ ጋ “ዐይኖች” ያዩትን እንዲያስታውሱ እግዚአብሔር እንደሚጠብቅባቸው አጽንዖት ይሰጣል። አ.ት፡ “ሕዝቡ በከፍተኛ ሁኔታ መሰቃየቱን እራሳችሁ አይታችኋል” (See: Synecdoche)

ዐይኖቻችሁ

ሙሴ ለእስራኤላውያን እንደ አንድ ሰው አድርጎ ይናገራቸዋል፣ ስለዚህ “የአንተ” የሚለው ቃል እዚህ ጋ ነጠላ ቁጥር ነው። (See: Forms of You)

ምልክቶቹንና እነዚያን ታላላቅ ድንቆች

“ምልክቶች” እና “ድንቆች” የሚሉት ቃላት ሁለቱም የሚያመለክቱት እግዚአብሔር በግብፅ ላይ የላካቸውን መቅሰፍቶች ነው። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ያደረጋቸውን ኃይለኛ ነገሮች ሁሉ” (See: Doublet)

እግዚአብሔር የሚያውቅ ልቦና፣ የሚያይ ዐይን ወይም የሚሰማ ጆሮ አልሰጣችሁም ነበር

ሕዝቡ ልብ፣ ዐይንና ጆሮ አላቸው። ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር ካዩትና ከሰሙት እግዚአብሔር ማን እንደሆነ፣ እንዴት እና ለምን እርሱን መታዘዝ እንደሚኖርባቸው እንዲያስተውሉ አላደረጋቸውም ይላል። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እንድታውቁ ልብን ሰጥቷችኋል

ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “ማስተዋል እንድትችሉ አድርጓችኋል” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)