am_tn/deu/29/01.md

878 B

እነዚህ ሙሴ እንዲናገር እግዚአብሔር ያዘዘው ቃሎች ናቸው

ይህ ሙሴ የሚናገረውን ቃል ያመለክታል።

በሞዓብ ምድር

ይህ እስራኤላውያን ወደ ከነዓን ምድር ከመግባታቸው በፊት ከዮርዳኖስ በስተምስራቅ የቆዩበት ስፍራ ነው። “በሞዓብ ምድር እያሉ”

በኮሬብ -- በኪዳኑ ውስጥ ተጨምረው የነበሩት ቃላት

እነዚህ ተጨማሪ ትዕዛዛት በአዲሱ ምድራቸው በሚቀመጡበት ጊዜ ሕዝቡ የእግዚአብሔርን ኪዳን በተሻለ ሁኔታ ተግባራዊ እንዲያደርጉት የተሰጣቸው ነበር። እነዚህ አዲስ ትዕዛዛት የሌላ ቃል ኪዳን ሳይሆኑ በመጀመሪያው ኪዳን ላይ ተጨማሪዎች ነበሩ።