am_tn/deu/28/65.md

972 B

ለእግርህ መርገጫ እረፍት አይኖረውም

እዚህ ጋ “ለእግርህ መርገጫ” የሚለው ሐረግ የሚያመለክተው ሙሉውን ሰው ነው። አ.ት፡ “የምታርፍበት ቋሚ ቤት ስለማይኖርህ ባለማቋረጥ ትቅበዘበዛለህ” (See: Synecdoche)

በዚያ እግዚአብሔር የሚንቀጠቀጥ ልብ፣ የሚደክም ዐይንና የሚያለቅስ ነፍስ ይሰጥሃል

ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “እግዚአብሔር እንድትፈራ፣ ተስፋ እንዳይኖርህና እንድታዝን ያደርግሃል” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

ሕይወትህ በፊትህ በጥርጣሬ ይንጠለጠላል

ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “ትኖር ወይም ትሞት እንደሆነ አታውቅም” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)