am_tn/deu/28/32.md

1.1 KiB

ወንዶችና ሴቶች ልጆች ለሌሎች ሕዝቦች ይሰጣሉ

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ወንዶችና ሴቶች ልጆችህን ለሌሎች ሕዝቦች እሰጣቸዋለሁ” ወይም “ጠላቶችህ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህን ይወስዷቸዋል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

ዐይኖችህ ቀኑን ሙሉ እነርሱን ይጠባበቃሉ፣ ሆኖም እነርሱን በመናፈቅ ይዝላሉ

እዚህ ጋ “ዐይኖችህ” የሚያመለክተው ሙሉውን ሰው ነው። አ.ት፡ “እነርሱን በመጠባበቅና ዳግመኛ ልታያቸው በመናፈቅ ትደክማለህ” (See: Synecdoche)

ምንም ብርታት በእጅህ ላይ አይኖርህም

እዚህ ጋ “ብርታት በእጅህ ላይ” የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር የሚያመለክተው ኃይልን ነው። አ.ት፡ “ስለጉዳዩ አንዳች ለማድረግ ኃይል አይኖርህም” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)